የሀገር ውስጥ ዜና

በጅማ ዞን የሩዝ ምርት መሰብሰብ ተጀመረ

By Feven Bishaw

November 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ እየለማ የነበረ የሩዝ ምርት መሰብሰብ ተጀመረ።

ምርቱ በአርሶ አደሮች፣ በማህበር በተደራጁ ወጣቶችና በባለሃብቶች የለማ ሲሆን ÷የዞኑ አመራሮች በተገኙበት በሸቤ ወረዳ መሰብሰብ ተጀምሯል።