የሀገር ውስጥ ዜና

በትምህርት ዘርፉ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

By Feven Bishaw

November 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፉ ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ከሚመለካታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የኮቪድ-19 ስርጭትን በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለመቀነስ ክትባቱ ለመምህራን እና በትምህርት ዘርፉ ላይ ለሚሰሩ አካላት ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።