አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቁ መሆኑ ተገለፀ፡፡
“እኔም የሰፈሬ ፖሊስ እና የሰላም ዘብ ነኝ” በሚል በከተማው በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የወረዳው አመራሮች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እና በመደራጀት በምሽት እና በቀን አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።