የሀገር ውስጥ ዜና

“በሀገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም” በሚል በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ሊካሄድ ነው

By Meseret Awoke

November 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕልውና ዘመቻውን የሚደግፍና የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሠላማዊ ሰልፍ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ሠላማዊ ሠልፉ “በሀገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሔድ ተገልጿል።

የሠላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ሃይል በዲሲ አስተባባሪ አቶ ጣሰው መላከሕይወት÷ ሠላማዊ ሰልፉ በኋይት ሐውስ ፊት ለፊት በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10 ሠዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በሠልፉ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የህወሓት አሸባሪ ቡድን በፈጸመው ጥቃት በግፍ የተጨፈጨፉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላትን በማስታወስ እንደሚዘከሩ ተናግረዋል።

ሠልፈኞቹ የሀገርን ሕልውና ለማስጠበቅ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሌሎችም የጸጥታ አካላት አጋርነታቸውንና ድጋፋቸውን ይገልጻሉ።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!