Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል ሕዝብ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ሕዝብ የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የህልውና ዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አስታወቁ፡፡

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ እንደገለጹት ÷ የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ማኅበረሰቡ ሀብት ንብረቱ ለዘመቻው እንዲውል ለመስጠት፣ አካባቢውን ነቅቶ ለመጠበቅና ተደራጅቶ ወደ ግንባር ለመትመም ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

አሁን የተጠራው የክተት ጥሪ ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገና የክልሉ ምክር ቤት ያወጣቸው አስገዳጅ ጥሪዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመው፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መደበኛ ሥራቸውን አቁመው የህልውና ዘመቻውን ሥራ የሚደግፉ ሥራዎችን ብቻ አተኩረው እንዲሠሩ፣ የሥራ ማስኬጃ በጀትም ከዚህ ሥራ ጋር ለተገናኘ አገልግሎት እንዲውል መወሰኑም ተመላክቷል፡፡

ይህ ማለት መሥሪያ ቤት ይዘጋል ማለት ሳይሆን ሠራተኛው እረፍት መውጣቱንም ትቶ ሁሉም ሠራተኛ በሰዓቱ ገብቶ የሚዘምተው ሠራተኛ እንዲዘምት ፣ ስንቅ የሚያዘጋጀው ስንቅ እንዲያዘጋጅና እንዲያቀብል የፕሮፓጋንዳ ሥራ የሚሠራውም እንዲሠራ በአጠቃላይ የህልውና ዘመቻውን የሚደግፍ ሥራ እንዲሠሩ ይደረጋል ነው ያሉት።

የትምህርት፣ የጤና እና የፍትህ ተቋማት ግን መደበኛ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version