አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል።
ም/ቤቱ ዛሬ በሚያካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በሀገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የሚቀርበውን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
የም/ቤቱን የመመስረቻ ጉባኤ እና 1ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ በማጽደቅ መደበኛ ስብስባ የሚጀምር መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!