Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የባቱ ከተማ ሰራተኞች ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚዘክር መርሃ ግብር አስበው ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባቱ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞችና አመራሮች የሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት በአሻባሪው ህወሓት የተጨፈጨፉበትን ዕለት ዘክረዋል፡፡
 
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ገዛህኝ ደጀኔ ዕለቱን ስናስብ የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር እና ከጠላት የተቃጣብንን ጥቃት በመመከት የጀግኖቻችንን የደም ካሳ ለመመለስ በቆራጥነት፣ በእልህና በአንድነት መስራት አለብን ብለዋል፡፡
 
የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ቀኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በአሸባሪው ህውሓት የተከዳበት ቀን በመሆኑ የቡድኑን ህልም ለማክሸፍ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክል ዝግጁ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version