አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የምድር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ እና የመከላከያ የብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል የሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ሰራዊቱ በወገኑ የተከዳበትን ዕለት ዘክረውት ውለዋል፡፡
በወቅቱም ህይወታቸውን ቤዛ ላደረጉ ጀግኖች ሰማዕታት የህሊና ፀሎትና የጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት ተከናውኗል ፡፡
አባላቱ እጃቸውን በደረታቸው ላይ ለ45 ሴኮንድ በማድረግ ሰማዕታቱን አስበዋቸዋል፡፡
የመከላከያ ብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል ማደራጃ ማስተባበሪያ ሃላፊ ብ/ጄኔራል ኢተፋ ራጋ÷የጀመርነውን ሃገራችንን የመታደግ ትግል በድል እንድናጠናቅቅ ሁላችንም ተቋማችን በሚሰጠን ግዳጅና ተልዕኮ መሰረት ከከፍተኛ አመራሩ አስከታችኛው ወታደር ድረስ በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ሁሉ በቁርጠኝነት፤ በትጋትና በታታሪነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
አባላቱ በሰጡት አስተያየት ፤ እንደ ጥንት አባቶቻችን አንድ በመሆን ለሚሰጠን ግዳጅና ተልዕኮ ከደጀኑ ህዝባችን ጋር በመሆን ሃገራችን ታፍራና ተከብራ ትኖራለች። በእኛ መስዕዋትነትም ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሚገኙ የስታፍ የሰራዊት አባላት እና ሲቪል ሰራተኞች የአሸባሪው የህውሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላት ላይ ያደረሰበትን የክህደት ጥቃት አንደኛ አመትለ45 ሰከንድ የህሊና ፀሎት በማድረግ አስበው መዋላቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!