የሀገር ውስጥ ዜና

የባሕር ዳር ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

By Alemayehu Geremew

November 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለማስቆም እንደሚዘምቱ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ሠራተኞች አስታወቁ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ በመሩት የውይይት መድረክ ÷ አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል እያደረሰ ያለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በሥልጣን ዘመኑም ሲያደርገው የነበረ እና ሥር የሠደደ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ድረስ አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል ታሪካዊ ጠላት በመሆኑ፥ ይህን ታሪካዊ ጠላት ለመቅበር የመንግሥት ሠራተኛው በግንባር መሠለፍ እንዳለበት ገልጸዋል።

በዚህም ቃላችንን ወደ ተግባር በመቀየር የአማራን አይደፈሬነት እና አይበገሬነት ልናሳይ ይገባል ብለዋል፡፡

የህልውና ዘመቻው የመጨረሻው ግብ አሸባሪውን የህወሓት ወራሪ ኃይል ከአማራ ክልል ማስወጣት ብቻ ሳይሆን ለአማራ ብሎም ለሀገር ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ማድረስ መሆኑንም ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም አካባቢያቸውን ነቅተው ለመጠበቅ፣ ሰርጎ ገቦችን ለማጋለጥ ብሎም ሀገር በምትፈልገው ሁሉ ለመደገፍና በቁርጠኝነት ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

አያይዘውም የአማራ ህዝብ በመደራጀት ራሱን መከላከል አለበት ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!