Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ አፍሪካውያን የህጻናት መብት እንዲከበር ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አፍሪካውያን እና መሪዎቻቸው የህጻናት መብት እንዲከበር ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ተናገሩ።

በአፍሪካ በሚከሰቱ ግጭቶች እና ጦርነት ምክንያት በሚጎዱ ህጻናት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የውይይት መድረክ ከህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም አፍሪካውያን የህጻናት መብት እንዲከበር መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

አያይዘውም ሃገራት ዕረፍት የሚነሱ ግጭቶችን መቀነስ ካልቻሉ ህጻናት ለዘመናት ተጎጂ ሆነው ይቀጥላሉም ነው ያሉት።

ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው ግጭት እና ጦርነትን ማስቆም ካልተቻለ ዘላቂ ልማት የሚባለው እንደማይታሰብም አንስተዋል።

በአፍሪካ በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚፈጸሙ ሲሆን፥ በተለይም ህጻናትና ሴቶችን ለጅምላ ጭፍጨፋ፣ ጾታዊ ጥቃትና መሰል ጉዳቶች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።

በተጨማሪም ለጉልበት ብዝበዛ፣ ጾታዊ ጥቃት እና ለህገ ወጥ ዝውውር እንደሚዳረጉም ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም ለሰው ህይዎት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ለበርካቶች ከቤት ንብረት መፈናቀል ምክንያት ነው።

ይህም በአፍሪካ የዜጎችን በተለይም የአህጉሪቱን ሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንንት ለማስጠበቅ ከወጡ ድንጋጌዎች ጋር የሚጣረስና ህጎች ላይ ስጋትን የሚደቅን ነው ተብሏል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version