አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ÷ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋዕትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት።
የሕወሓት የሽብር ቡድን የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በቅስቀሳ የመጣውን የህዝብ ኃይል ለማስተናገድ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት እንዳልነበርም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ከዛ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡
አጠቃላይ ህዝቡ ለሠራዊቱ ያለው ድጋፍ አሁን ካለው በላይ ሊጠናከር ይገባል ያሉት ዶክተር ዐቢይ÷ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ዋጋ ለመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ካለምንም ጥርጥር ኢትዮጵያ ጦርነቱን ታሸንፋለች ሲሉ ጠቅላይ ሚሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
ለማሸነፍ ቁልፉ እጃችን ላይ ነው ያለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷አንድ መሆን ቀን ከሌት መስራት፣ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆንን አካተው ገልጸዋል፡፡
የምናሸንፍበት እድል ግን የምናገኘነው ከጠላት መሆኑን ጠቅሰው ÷ መረጃ እና ፕሮፓጋንዳ በመጠቀም ማሸንፍ እንደሚቻል አንስተዋል፡፡
ጦርነት የፖለቲካ እሳቤ ማስጠበቂያ የመጨረሻ መንገድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ውጊያ በየትኛውም ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ገልፀው ጦርነቱን ግን ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ አትጠራጠሩ ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!