የሀገር ውስጥ ዜና

በቀይ አፈር ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

November 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን በደቡብ ኦሞ ዞን በበናፀማይ ወረዳ በቀይ አፈር የመጀመሪያ ደረጃትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በፕሮግራሙ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።

የፋውንዴሽኑ መስራች ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ከተማሪዎች እና ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!