Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሼህ ሐሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማና የክልሉ የጤና ቢሮ ሐላፊ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼህ ሐሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል ጎበኝተዋል ።

በጉብኝታቸውም የሲቲ እስካን ፣የእናቶችና ህፃናት የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ማዕከል ፣ እና የጅግጅጋ ደም ባንክና ቲሹ ማዕከልን ተመልክተዋል ።

አዲሰ ቢኤስ አይ ኤስ የተሰኘ የደም ባንኩን አገልግሎት ከማንዋል ወደ ዲጅታል አገልግሎት የቀየረ አሰራርና አዲስ አውቶሜሽን ማሽን ስራንም አስጀምረዋል ።

ዶክተር ሊያ ታደሰ የሪፈራል ሆስፒታሉ አጠቃላይ 350 አልጋ ይዞ አገልግሎት መስጠቱ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በአንድ አመት ውስጥም ለ179 ሰዎች የተገለገሉበት የኩላሊት እጥበት ህክምና ማዕከልም ጥሩ ስራና መልካም ምሳሌ መሆኑን ተናግረው ÷ የሪፈራል ሆስቲታል ተቋሙን ከዚህ በበለጠ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የማጠናከርና የእገዛ ስራዎች እንደሚሰሩ አንስተዋል ።

የጅግጅጋ ደም ባንክ አገልግሎቱን ከጥራትና ከምቹነት ጋር ለማጣመር ዛሬ የተጀመረው የዳታ መረጃን ዲጂታይዝ የማድረግ ስራ የደም ናሙና መመርመሪያ ማሽኑ በምስራቁ ክፍል ላሉ ስድስት የደም ባንኮች አገልግሎት የሚሰጥና የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version