አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን መንግስት ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የሰራባ ዳብሎ ቀበሌ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
አርሶ አደሮቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ አሸባሪው የህውሃት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከትና በግንባር ለመዋጋት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አርሶ አደሮቹ የአማራ ክልል መንግስት የህወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በየትኛውም መልኩ የጥፋት ሀይሉን ለመዋጋት የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው መስዋዕት ለመክፈል ቁርጠኛ ነን ያሉት አርሶ አደሮቹ÷ ይህንም በተግባር እናረጋግጣለን ብለዋል።
አሸባሪው ህውሃት ከመጣ ህፃን አዋቂ ብሎ ስለማይመርጥ የቻለ ግንባር በመዝመት አቅሙ ያልፈቀደ ደጀን በመሆን፣ የጦርነቱ አካልና ጀብድ እንዲፈፅም ጥሪ አቅርበዋል አርሶ አደሮቹ።
መንግሥትም አስፈላጊውን የዘመቻ ግብዓት እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!