የሀገር ውስጥ ዜና

የጀርመን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

October 30, 2021

 

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 20፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ከ50 በላይ የጀርመን ኩባንያዎች እና ባለድርሻዎች በኢትዮጵያ ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ውይይት አደረጉ።

የጀርመን-አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር ፥ በጀርመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በጋራ ያዘጋጁት መድረክ ነው።

የጀርመን እና የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ፣በንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ መስፋት አለበት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የህግ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የጀርመን ኩባንያዎችን አድንቀው፤ ሌሎችም የነሱን ፈለግ እንደሚከተሉ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን፥ መንግስት ይበልጥ በሩን መክፈት እና በኢንቨስትመንት ፖሊሲ ላይ በጀርመን ባለሀብቶች የሚነሳው ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል ብለዋል።

የጀርመን-አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክላውዲያ ቮስ የጀርመን ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ያሉት የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ከ250 ሺህ በላይ ኩባንያዎች የጀርመን-አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር አባል መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!