አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ከ333 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ገቢው የተገኘው ወደተለያዩ የዓለም አገራት ከተላከው 88 ሺህ ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ነው ተብሏል፡፡
የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ144 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ ማሳየቱን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሳህለማርያም ገብረመድህን ተናግረዋል።
በዘርፉ የተካሄዱት የፖሊሲ ማሻሻያ እና ሪፎርም ለገቢው ማደግ የጎላ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!