አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና ቡድናቸው ከ‘ካርዳኖ’ እና ‘ኢቴሪየም’ መስራች ቻርለስ ሆስኪንሰን ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉትን ዋና ዋና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ምርምር ፣ በአቅርቦትና በሀገሪቱ የዲጂታይዜሽን ስራዎች ላይ ለማካተት ያለውን ዝግጁነት አስረድተዋል።
ሆስኪንስ በበኩላቸው ÷ የፋይናንስ ዝውውርን የሚያግዝ የቴክኖሎጂ አቅም እና በኩባንያው በሚቀርቡት የተለያዩ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች እንዲሁም የኩባንያው የአፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ኢትዮጵያ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ስለመጀመር ውይይት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!