የሀገር ውስጥ ዜና

ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

By Meseret Awoke

October 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ ለኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማእከል የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የወጋገን ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ባንኩ ያደረገው ድጋፍ ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

የልብ ህሙማን ማእከሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ህሩይ አሊ ባንኩ ከማእከሉ ግንባታ ጀምሮ እስካሁን ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው እንደ ወጋገን ባንክ ያሉ ተቋማትና ማህበረሰቡ ለማዕከሉ የሚያደርገው ድጋፍ ህክምና በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ህጻናትን ችግር ይቀርፋል ብለዋል።

የ1 ሚሊየን ብር ቼኩንም የልብ ማእከሉ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ ከባንኩ የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ተረክባለች።

በቅድስት አባተ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!