የሀገር ውስጥ ዜና

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከሃንጋሪ ዩኒቨርሲቲ ጋራ በትብብር ለመስራት ተስማማ

By Feven Bishaw

October 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከሃንጋሪ የግብርና እና ህይወት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ ጥቅምን በዓለም አቀፋዊ አካዳሚክ ትብብር ለማሳደግ ያለመ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ሁለቱም ተቋማት በምርምር፣ በትምህርት እና በመምህራን ልማት ዙሪያ ተባብረው ለመስራት ተስማምተዋል፡፡