Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከሃንጋሪ ዩኒቨርሲቲ ጋራ በትብብር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከሃንጋሪ የግብርና እና ህይወት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ ጥቅምን በዓለም አቀፋዊ አካዳሚክ ትብብር ለማሳደግ ያለመ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ሁለቱም ተቋማት በምርምር፣ በትምህርት እና በመምህራን ልማት ዙሪያ ተባብረው ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን ተግባራዊ በሚያደርጉበት ወቅት ሁለቱ ተቋማት የተማሪዎች፣ መምህራን ልውውጥ፣ ጥናት እና ምርምር እንዲሁም የጋራ ጉብኝት በማድረግ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version