የሀገር ውስጥ ዜና

የምዕራብ ጎጃም ዞን በደሴ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

By Alemayehu Geremew

October 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን በአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለተጠለሉ ዜጎች የሚውል 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊና የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ወንድሜነህ ልየው እንደገለጹት፥ ድጋፉ በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ‘አለኝታነታችንን ለማሳየት የተደረገ ነው’።

የተደረገው ድጋፍ ዱቄት፣ በቆሎ፣ አልባሳት እና ሌሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በወራሪው የህወሓት አሸባሪ ቡድን ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ ማሩ ‘ለወገን ደራሹ ወገን ነው’ በሚል የምዕራብ ጎጃም ዞን ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።