አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤጂንግ ማራቶን ውድድር የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ስርጭት በሀገሪቱ በፈጠረው ስጋት ምክንያትለሌላ ጊዜ መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡
ቻይና ኮቪድ-19 በሀገሪቱ ለሚካሄደው ማራቶን ውድድሩ ስጋት እንዳይሆን እና የሥርጭት ሂደቱን ለማስወገድ በርካት ስራዎች ስትሰራ መቆየቷ ተመላክቷል፡፡
ይሁን እንጂ በቻይና በዛሬው ዕለት ብቻ 39 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ተከትሎም የቤጂንግ ማራቶን ውድድር የሚካሄድበት ቀን እስኪገለጽ ድረስ ለሌላ ጊዜ መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል፡፡
ውድድሩ የተራዘመውም ተሳታፊ ስፖርተኞች፣ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች የቫይረሱ ስጋት ሳይኖርባቸው ውድድሩን በስኬት እንዲያካሂዱ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት በተካሄዱ ቤጂንግ ማራቶን ውድድሮች 30 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ይሳተፉ እንደነበር መጠቆሙን ፍራንስ-24 ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!