አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር ተወያዩ።
መሪዎቹ በሁለትዮሽ ፣ ቀጣናዊ እና አለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተነገረው።
የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋርም ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ከዚህ ባለፈ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንደሚወያዩ ተጠቁሟል።
እንዲሁም ከህብረቱ ጎን ለጎን በሚካሄዱ ውይይቶች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይሳተፋሉ ተብሏል።