አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከድሬዳዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ላስ ዴሬ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ከንጋቱ 11 ሰዓት አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ በ5 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ7 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።
በዚህ አደጋ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር በንብረት ላይም ጉዳት ማጋጠሙ ነው የተነገረው።
አደጋው ያጋጠመው በ3 ሚኒባስ እና በ2 ትራከር መኪኖች መሆኑን ፓሊስ ማስታወቁን ከድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።