የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ጎንደር ዞን ዘማች የሚሊሻ አባላት አሸኛኘት ተደረገላቸው

By Feven Bishaw

October 24, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስር ከሚገኙ 18 ወረዳዎች የተውጣጡ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ግንባር ለመዝመት በነፋስ መውጫ ከተማ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ሀገር እና ሕዝብ የጣለባቸውን አደራ በጀግንነት እንዲወጡ፤ ደጀን የሆነው ሕዝብ፣ የዞን አስተዳደሩ እና በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት መዋቅር ደግሞ የዘማች ቤተሰቦችን በኃላፊነት እንዲንከባከብ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኅላፊ አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ÷ከጉና ተራራ ግርጌ ከጋፋት ራስጌ የመነጫውን ጥንታዊ ታሪካችሁን አስጠብቃችሁ እንደምትመለሱ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡