የሀገር ውስጥ ዜና

በቦረና አካባቢ በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ እንስሳት የሚውል መኖ ድጋፍ ተደረገ

By Feven Bishaw

October 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በቦረና አካባቢ በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ እንስሳት የሚውል መኖ ድጋፍ አደረጉ።

በአካባቢው በድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ዜጎችን ለማገዝ ነው ክፍለ ከተማው ከ4 ሺህ በላይ ቦንዳ የእንስሳት መኖ እንዲሁም ለተወሰነ ወራት የሚያገለግል የውሃ ቦቴ መኪናም ጭምር ድጋፍ ያደረገው፡፡