የሀገር ውስጥ ዜና

በጣሊያን እና በግሪክ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ተካሄደ

By Tibebu Kebede

October 23, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ተካሄደ።

በኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለመከላከያ ሰራዊት “እኔ ለሀገሬ ሀገሬም ለኔ” በሚል መሪ ቃል የሚሰበሰበው የገንዘብ ድጋፍ በጣሊያን ሮም፣ በሚላን፣ ቱሪን እና በግሪክ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በጣሊያን ባለሙሉ ስልጣን ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በአሁኑ ወቅት ከምንጊዜውም በላይ ከሀገራቸው ጎን መቆም እንደሚገባና ድጋፋቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!