የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

October 22, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር ራሁፍ ማዙሃ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ።

በኢትዩጵያ ውስጥ ሰለመገኙ ሰደተኞች እና በህወሓት የሽብር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ቁጥራቸው የጨመረው የተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ በጋራ መክረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በትግራይ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች በወያኔ የሚደርስባቸው ጫና እና ለኤርትራውያን ስደተኞች በአማራ ክልል አዲስ እየተሰራ ስላለው መጠለያ አሁናዊ ደረጃ ለረዳት ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በሱዳን የሰደተኞች ካምፕ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች በሀገር ቤት ከሰሩት ወንጀል ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት እንደሚያሳስባቸው አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በበኩላቸው የአቶ ደመቅን ስጋት ትኩረት የሰጡት እና ከመንግስት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ስደተኞችን በጋራ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!