የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

By Feven Bishaw

October 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያ ጉባኤ አቶ ኦርዲን በድሪ በድጋሚ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን የክልሉን ህዝብን በቅንነት ለማገልገል ቃለ-መሐላ መፈፀማቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡