የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ምክር ቤት ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን አፈጉባኤ አድርጎ መረጠ

By Feven Bishaw

October 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው ምክር ቤቱ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን ዋና አፈጉባኤ እንዲሁም አቶ አሪፍ መሀመድ አዱስን ደግሞ ምክትል አፈጉባኤ በማድረግ መምረጡን የሀረሪ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡