አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ርዕሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በአማራ ክልል እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አስመልክቶ ለአምባሳደሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሽብር ቡድኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!