የሀገር ውስጥ ዜና

ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

By Meseret Awoke

October 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ከኢትዮጵያውያን ላሰባሰበችው 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ እውቅና የመስጠትና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የበጎ ፍቃድ አምባሳደሯ ለአንድ ወር ያክል በቆየችባቸው ከተሞች ላይ ከፍተኛ ፍቅርንና እንክብካቤን በመስጠት ለልብ ህሙማኑ ሕፃናት ድጋፍ ለመሆን በቀና ልብ ለተሳተፉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ብሎም በአሜሪካ ለሚገኙ ተቋማት ድርጅቱ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ድጋፉ በሕመሙ እየተሰቃዩ ለሚኖሩ ሕፃናት የሕክምና ግብዓትን ከሟሟላትም በላይ የነገ ተስፋ ሰጪ እና ምሳሌ መሆን የሚችል ሰናይ ተግባር መሆኑንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!