አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ድሮኖች የግብርናውን ሥራ እያቀላጠፉ ነው፤ እውቅናቸውም እየጨመረ መጥቷል ተባለ፡፡
ለማነጻጸር ÷ አንድ ሰው በቀን 4 ሄክታር ማሳ የአረም ማጥፊያ መድሃኒት ወይም ማዳበሪያ የመርጨት አቅም ሲኖረው፣ አንድ ድሮን ግን በቀን 1 ሺህ 215 ሄክታር ማሣ የአረም ማጥፊያ መድሃኒት ወይም ማዳበሪያ ረጭቶ የማጠናቀቅ ብቃት አለውም ተብሏል፡፡
የቻይና የግብርና ማሽነሪዎች ሥርጭት ማኅበር መረጃ እንደሚያመላክተው ÷ በፈረንጆቹ 2017 ከ1 ሺህ የሚያንሱ ለግብርና ስራ የሚውሉ ድሮኖች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2020 በሀገሪቷ ያለው ለግብርናው ዘርፍ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ድሮኖች ፍላጎት ቁጥር እጅግ አሻቅቦ ከ15 ሺህ በላይ ድሮኖች መሸጣቸው ነው የታወቀው፡፡
ድሮን አምራቾች ÷ ቴክኖሎጂው ፣ የበለጠ የሚያመርቱ እና የሚያተርፉ ገበሬዎችን ይፈጥራል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል ሲል የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡
በዓለማየሁ ገረመው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!