Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአሸባሪው ህወሓት ሀሰተኛ መረጃ በአፋር የዳጉ የመረጃ ስርዓት ይመክናል – የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የዳጉ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት የአሸባሪው ህወሓት ሀሰተኛ መረጃን ለማጋለጥና ለማምከን እንደሚያስችላቸው የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት÷ በአፋር ክልል ያለው ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት አፋሮች ጥልቅና የተረጋገጠ መረጃ ይቀባበላሉ።

ከክልሉ ነዋሪዎች “ዳጉ” የተጣራና የተረጋገጠ መረጃ የሚንሸራሸርበት ስርዓት በመሆኑ “ሳንሰማው የሚያልፈንና በሀሰን የሚያሳስተን ነገር የለም” ይላሉ።

በተለያዩ መንገዶች አሁን ላይ ለሚናፈሰው በሬ ወለደ ወሬ አፋሮች በ“ዳጉ” የመረጃ ልውውጥ ስርዓት እውነታውን ለመረዳት ጊዜ የማይወስድባቸው መሆኑን ይናገራሉ።

በመሆኑም አሁን ላይ አሸባሪው ህወሓት በሚያሰራጨው የውሸት ፕሮፓጋንዳ በአፋር የሚደናገር እንደማይኖር ነው አቶ አሊ የተናገሩት።

አፋሮች የቤት እንስሳቶችን ደህንነት ሳይቀር በሚጠያየቁበት የዳጉ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት የአሸባሪው ህወሓት ውሸት እንደሚመክን አቶ አሊ ያብራራሉ።

እንዲሁም ነዋሪዎቹ “በዳጉ የመረጃ መቀባበያ ስልታችን ከጥንት እስከ ዛሬ ኖረንበታል ፤ በቀጣይም መረጃ እየሰጠን የምንቀበልበት አይነተኛ መሳሪያችን ሆኖ ይቀጥላል” ብለዋል።

አሁን ላይ ዘመን አመጣሽ የመረጃ ማድረሻ መንገዶች እየተበራከቱ ቢሆንም፤ አፋሮች በ“ዳጉ” መረጃ እያቀበሉ፣ እየተቀበሉና እያጣሩ እውነታውን በፍጥነት እየተረዱ እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት።

አሸባሪው ህወሓት ሀገር ለማፍረስ፣ ህዝብ ለማፈናቀልና ዘረፋ ለመፈፀም በሚያናፍሰው “የተቀነባበረ ሴራ ሳንደናገር በመጣበት ሁሉ ለመመከት ተዘጋጅተናል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version