Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪና ለሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪና ለሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጥቷል፡፡
 
ምክር ቤቱ ባካሄደው 4ኛ ዙር 9ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በኩል የቀረበውን የምክትል አስተዳደሪና ሌሎች አመራሮችን ሹመት መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
 
ዋና አስተዳዳሪ ሆነውየተሾሙት አቶ አብዮት ደምሴ÷ ህብረተሰቡ ውስጥ እየተነሳ ያለዉን የመልካም አስተዳደርና የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ እንዲሁም የህዝቡን ችግር ለመፍታት ተቀናጅተን መስራት አለብን ብለዋል።
 
የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ምስጋና ዋቃዮ በበኩላቸው÷አዳዲስ የተሾሙ አመራሮችም ከቢሮ ሥራ በተጨማሪ የህዝቡን ችግር በመለትና መፍትሄዎችን በማመንጨት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
ከተፎካካሪ ፖርቲዎች ጋር እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
 
በዞኑ የነበሩትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ አዲሱ ካቢኔ ተግቶ እንዲሰራ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡
 
በማስተዋል አሰፋ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version