አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የ5ኛው ትውልድ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 450 ሚሊየን መድረሱን የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የደንበኞች አገልግሎት በተገቢው ሁኔታ የሚያሳልጡ 1 ነጥብ 16 ሚሊየን በላይ የ5 ጂ ኢንተርኔት ማዕከላት መኖራቸውንም ሚኒስቴሩ አመላክቷል፡፡
ከዚህ ባለፈም በሀገሪቱ ያለውን የኢንተርኔት አገልሎት ለማዘመን በተሰራው ስራ 200 ሚሊየን ለሚሆኑ አባ ውራዎች የጊጋ ባይት ኦፕቲካል መስመር ዝርጋታ መከናወኑ ነው የተገለጸው፡፡
ይህን ተከትሎም ባለፉት 9 ወራት ከቴሌከም ዘርፉ የተገኘው ገቢ ካባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 28 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
ምንጭ÷ ሺንዋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!