አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር እና በጎንደር ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላት የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፎች አድርገዋል።
በድጋፉ ከተካከቱት መካከል ከ50 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ 60 ካርቶን የንፅህና መጠበቂያ፣33 ካርቶን ሶፍት፣2 ሺህ220 የእጅ ጓንት እና 60 ሽርጦችን መሆናቸው ተመላክቷል።
ድጋፉን ያስረከቡት የሰሜን ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ እና የግንባር ህዝባዊ ድጋፍ አስተባባሪ አቶ አንዳርግ ዘነበ እንደተናገሩት ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ በተደረጉ ማንኛውም አይነት ውጊያዎች ሴቶች የሌሉበት አውደ ውጊያ የለም ብለዋል።
አሸባሪው እና ወንበዴው የህውሓት ቡድን በሰሜን ጎንደር ዞን ጥቃት ለማድረስ በመጣበት እና የእፍረት ካባውን ተከናንቦ ድባቅ በተመታበት ጊዜ በማይጠብሪ ግንባር የሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የምዕራብ ዕዝ ሴቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ሌ/ኮ አትክልት ይግዛው፥ ሴትነት ወደር የማይገኝለት ፀጋነው በሚገኙት ድሎች ሁሉ ሴቶች ግንባር ቀደም ተሰላፊዎች ናቸው ብለዋል።
በግንባሩ ከሚገኙ ክ/ጦሮች መካከል የሴቶች ጉዳይ አስተባባሪ የሆኑት ሻ/ል እልፍነሽ ፍቃዱ እና መ/አ ምትክ ንጉሴ በበኩላቸው ፥ ከአራቱም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሴት የሠራዊት አባላት ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬውም ዕለት ለተደረገላቸው ድጋፍ በማይጠብሪ ግንባር በሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላት ስም ማመስገን እንወዳለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
35
Engagements
Boost Post
32
1 Comment
2 Shares
Like
Comment
Share