Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አዲስ አበባ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ሀገራት እና መንግስታት መሪዎች እንዲሁም የሌሎች ሀገራት መሪዎች ለአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የዘንድሮው የጉባኤው መሪ ቃል “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት” የሚል ነው።

ለጉባኤው የህብረቱ አባል ሀገራት እና መንግስታት መሪዎች ከአርብ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ነበሩ።

በአጠቃላይ በጉባዔው ላይ የ31 የአፍሪካ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች፣ 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የሰባት ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የሀገራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ቀዳማዊት እመቤቶች እንደሚሳተፉ ነው የሚጠበቀው።

በተጨማሪም የተመድ ዋና ፀሃፊን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሀላፊዎች እና የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል።

በምስክር ስናፍቅ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version