አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በመተከል ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎችን ድጋፍ ለማድረግ ከ55 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመያዝ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።
ፕሮጀክቱ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎችን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ዕቅድ ባለድርሻ አካላት በተገኙበትይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አስተባባሪነት አኒ ኢትዮጵያ እና ሚስሚዶ የተሰኙ ግብረ ሰናይ ደርጅቶች በወንበራና ድባጢ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ 55ሚሊየን 647ሺ 864 ብር በጀት መያዙ ነው የተገለጸው፡፡
በፕላን ኢንትርናሽናል ኢትዮጵያ የመተከል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ ብርሃን÷በተመረጡ ወረዳዎች ለ56 ሺህ 791 የህብረተሰብ ክፍሎችን በውሃ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በህጻናት ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ትኩረት የሚሰጥባቸው ተግባራት መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ ስራውን ለማከናወን የአንድ ዓመት የቆይታ ጊዜ እንደሚኖረው አቶ መልካሙ ገልጸዋል።
በእቅድ ትውውቅ መርሃ ግብሩ የዞንና የወረዳ አመራሮች የተገኙ ሲሆን÷ ለዕቅዱ ስኬት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት ተላልፏል።
ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት በማንዱራና ዳንጉር ወረዳዎች ተፈናቃዮች በርካታ ድጋፎችን ማበርከቱን ከመተከል ዞን ኮሙዩኑኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!