አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል፡፡
በጉባኤው አቶ አክሊሉ ለማ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተመርጠዋል።
ምክር ቤቱ ወይዘሮ ካሰች ኤሊያስን የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ እንዲሁም ወይዘሮ ጤናዬ ትሩንጎ በነበሩበት የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል፡፡
አቶ አክሊሉ ለማ አዲሱ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር የመምሪያ ኃላፊዎችን መርጠው ምክርቤቱ ያፀደቀላቸው ሲሆን ÷በሚቀጥሉት ጊዜያት ከሰፊው ሕዝብ ጋር በመቀናጀትና በትብብር ለመስራት ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም በዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር የክልል ምክርቤት አባላት ስንብት ተደርጓል።
በተመሳሳይ የጋሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት የስራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ወይዘሮ አብዮት አባይነህን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ዘውዴን የዞኑ ዋና አሰተዳዳሪ አድርጎ ሹሟል፡፡
በዋና አስተዳዳሪው እጩ አቅራቢነት ከኢዜማ ፖለቲካ ፓርቲ አቶ መለሰ ጮራ የዞኑ የሳይንስና የቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ተሾመዋል፡፡
በመለሰ ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!