አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫውን እንግሊዝ ካደረገው ቢግ ዊን ፋውንዴሽን የቦርድ አባላት ጋር ተወያዩ።
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 የመቀንጨር ችግርን ለማስወገድ ለምታደርገው ጥረት ፋውንዴሽኑ የሚያደርገውን ድጋፍ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድንቀዋል።
አቶ ደመቀ አያይዘውም ቢግ ዊን ፋውንዴሽን በሀገሪቱ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ የሚያደርገው እገዛ ተጠቃሽ መሆኑንም አንስተዋል።
የቢግ ዊን ፋውንዴሽን የቦርድ አባላት በበኩላቸው መንግሥት በሁሉም ዘርፎች የሚወስዳቸው ትርጉም አዘል እርምጃዎች የሚያበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የቦርድ አባላቱ በሃገሪቱ ትርጉም ያለው ውጤት እንዲመዘገብ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision