Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግብርና ምርቶችን በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለሕብረተሰቡ ማቅረብ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ሽንኩርትና ሌሎች የግብርና ምርቶች በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡
ከ2መቶ 92 ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩርት ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወደ ከተማዋ መግባቱን የከተማ አስተዳደሩ ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ገልጿል።
ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ፣ ከከንቲባ አዳነች አበቤ እና የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል የአርሶ አደሮች ማሳን በጎበኙበት ወቅት የሽንኩርት እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲገባ መግባባት ላይ መድረሱ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት በመጀመሪያ ዙር ከ2መቶ 92 ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩርት ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በሸማች ማህበራት አማካኝነት ለህብረተሰቡ እንዲሰራጭ ርክክብ መካሄዱን የኤጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አረጋ ገልጸዋል።
በአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ባሉ የግብይት ማዕከላት የሽንኩርትና ሌሎችም የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋል ብለዋል።
በቀጣይ ቀናት ከ5መቶ 60 ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩርት ከአርሶ አደሮች እንደሚቀርብ አቶ ሲሳይ መግለጻቸዉን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክረታሪያት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version