Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ሕሙማን ቁጥር ከ8 ነጥብ 42 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአፍሪካ በኮቪድ 19 ቫይረስ የተያዙ ሕሙማን ቁጥር 8 ሚሊየን 426 ሺህ 107 መድረሱን የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል አስታወቀ፡፡

በቫይረሱ ከተጠቁት ውስጥ የ215 ሺህ 467 ሕሙማን ሕይወት ማለፉንም ነው የማዕከሉ መረጃ ያመላከተው፡፡

ወረርሽኙ ከጠናባቸው የአፍሪካ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ 2 ሚሊየን 916 ሺህ 179 በቫይረሱ የተጠቁ ሕሙማንን በመመዝገብ ቀዳሚ ሆናለችም ነው የተባለው፡፡

እስካሁን ድረስ በደቡብ አፍሪካ 88 ሺህ 587 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሕይወት እንዳለፈም ነው የታወቀው፡፡

በአህጉሪቷ÷ ሞሮኮ 941 ሺህ 863 ፣ ቱኒዚያ ደግሞ 710 ሺህ 773 ሕሙማንን በመመዝገብ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ለማዕከሉ ሪፖርት ያደረጉ ሀገራት ሆነዋል፡፡

እንደሚታወሰው በዓመቱ አህጉሪቷ ክትባቱን ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ካደረገች በኋላ ካለፉት 2 ወራት ወዲህ በርካታ ሀገራት ክትባቱን እንዳገኙና ወረርሽኙ ከዚህ እንዳይከፋ በዘመቻ መልኩ አፋጣኝ ክትባት እየሰጡ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡

መልካሙ ዜና የሚሆነው 7 ሚሊየን 801 ሺህ 688 ሕሙማን ከቫይረሱ አገግመዋል – የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ሪፖርትን አመላክቶ የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version