ፋና ስብስብ

6 ሺህ ጥንዶች የተካፈሉበት የሰርግ ስነ ስርዓት በደቡብ ኮሪያ ተከናወነ

By Tibebu Kebede

February 07, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን ቻይና ያደረገው የኮሮኖ ቫይረስ ለበርካቶች ስጋት ቢሆንም በደቡብ ኮሪያ ግን በርካቶችን ያሰባሰበ የሰርግ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

በሰርግ ስነ ስርዓቱ ላይ 30 ሺህ ሰዎች የታደሙ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 6 ሺህዎቹ አዲስ ተጋቢዎች ናቸው ተብሏል።

ቀሪዎቹ ደግሞ ቃላቸውን ያደሱ እና ታዳሚዎች ብቻ መሆናቸውን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ከተለያዩ ሃገራት የመጡት ጥንዶችም የሰርግ ስነ ስርዓታቸውን ቺኦንግ ሺም በሚገኘው የዓለም የሰላም ማዕከል ቤተ ክርስቲያን አከናውነዋል።

የቤተክርስቲያኗ ሠራተኞችም የፊት ጭምብልን ጨምሮ የህክምና ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት እና የሙሽሮችን የሙቀት መጠን በመለካት የሰርግ ስነ ስርዓቱ እንዲከናወን አድርገዋል።

አዲሱን ቫይረስ ለመከላከል በሠርጉ ሥነ ሥርዓት ላይ የተዘጋጁ ጭምብሎችን ያደረጉ ተጋቢዎች ግን ጥቂቶች ብቻ እንደነበሩ ነው የተገለጸው።

ምንጭ፡-ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision