Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል መንግስት ምስረታ ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሔደ ነው

 

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የተካሄደውን 6ተኛ አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ነው በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የሚመሰረተው።

272 መቀመጫዎች ያለውና ዛሬ የሚካሔደው የክልሉ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ ይመርጣል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የክልሉን ርዕሰ-መስተዳድር የሚመርጥ ሲሆን የተመረጡት ርዕሰ መስተዳድርም የክልሉን መንግስት አስፈጻሚ አካላት ሹመት በምክር ቤቱ አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉን አዲስ መንግስት የምስረታ ጉባኤ ለመታደም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የመጡ እንግዶች ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version