የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በምእራብ አርሲ ዞን ሴሮፍታ የግብርና ምርጥ ዘር ማባዣን ጎበኙ

By Feven Bishaw

October 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በምእራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ሴሮፍታ የግብርና ምርጥ ዘር ማባዣን ጎበኙ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ የሁለቱ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችንና ሚኒስትሮችን ያካተተ ልኡክ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የግብርና ምርት እየጎበኙ ይገኛሉ።