Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቢሮው በሩብ ዓመቱ 13 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 11 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ያቀደው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከዕቅዱ በላይ 13 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለጸ።
ገቢው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች እና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው ሲሉ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ገልጸዋል፡፡
በእቅድ ዝግጅት ምዕራፍ የተጠናከረ ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በመሰራቱ፣ የሕ ማስከበር ሥራዎች በመሠራታቸው እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ለግብር ከፋዮች መሰጠቱና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ መዋላቸው ለውጤቱ መገኘት አስተዋፅኦ አድርገዋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ÷ በታማኝነት ግብር የሚከፍሉ እንዳሉ ሁሉ የሚያጭበረብሩ መኖራቸውን ጠቁመው÷ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ግብር በአግባቡ ባልከፈሉ ላይ በተጣለ ቅጣት 800 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ጠቁመዋል።
በማጭበርበር፣ ደረሰኝ ባለመጠቀምና ሀሰተኛ ደረሰኝ በመጠቀም የተያዙ 100 ግብር ከፋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረው÷ ባልተገባ መንገድ ከስነ ምግባር ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 20 የቢሮው ባለሙያዎች በአስተዳደራዊና በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ከግብር ከፋዩ ጋር ሲደራደሩ እጅ ከፍንጅ የተያዙ በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጉን ተናግረዋል።
አሁንም ሀሰተኛ ደረሰኝ መጠቀም፣ ያለደረሰኝ መሸጥ እና የማጭበርበር ተግባራት እንደሚፈጸሙም ነው አቶ ሙሉጌታ የተናገሩት፡፡
በሸማቹ በኩልም ደረሰኝ ያለመጠየቅ እና ያለደረሰኝ የመግዛት ችግሮች እንደሚስተዋሉም ጠቁመዋ፡፡
የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ግብር በመክፈል ከቅጣት እንዲጠበቁ ጥሪ አስተላልፈዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version