Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎቹን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 1 ሺህ 127 ተማሪዎችን ነው፡፡
የውስጥ እና የውጪ ጫናዎችን ተቋቁመን ለዚህ ቀን በቅተናል ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ 5 የምርምር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው÷ ትምህርት ሲስፋፋ የግጭት ዕቅድ ይዘጋል፤ ሌሎች ሀገራትም ለዘርፉ በሰጡት ትኩረት ነው ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱት ብለዋል፡፡
የዛሬ ተመራቂዎችም በተማራችሁት ትምህርት ሀገራችሁን ለመለወጥ ጥረት ማድረግ ይኖርባችኋልም ነው ያሉት፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው የምረቃ መርሃግብርም ለመጀመሪያ ጊዜ 85 ምሩቃንን በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለአንጋፋው ፖለቲከኛ፣ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኝ እና ጸሐፊ ለአቶ ሌንጮ ለታ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
የክር ዶክተር ሌንጮ ከዩኒቨርሲቲው ለተሰጣቸው እውቅና አመስግነው÷ በሀገር ደረጃ የተገኘውን ድል መንከባከብና የቀሩ ጉዳዮችን በመመካከር ማስተካከል ይቻልል ብለዋል፡፡
የተገኘውን ውጤት አሳንሶ ማየት የለብንም÷ ትናንት የነበርንበትን በማስተዋል ይህንን እንድናገኝ መስዋዕት ለሆኑ እና እዚህ ላደረሱን ክብር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version