አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ዕድል የሚወስነው የአገሩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ሌላ ምንም ምድራዊ ሃይል ሊኖር እንደማይችል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ አስገነዘቡ።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፥ በትህነግ ቡድን የእብሪት ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ደጋፍ ለማድርግ ኢትዮጵያውያን ባዘጋጁት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የአገራቸውን መፃኢ ዕድልና ጉዞ ለመወሰን ህጋዊ ኃይልና ሉዓላዊ መብት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ብቻ መሆናቸውን አስምረውበታል።