Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡
በዚህም ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከጥቅምት 29 እስከ ሀዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡
የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ባዘጋጀው የንቅናቄ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
ከ617 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ዝግጁ መሆናቸውን የኤጀንሲው የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ገልጸዋል፡፡
ፈተናው የጸጥታ ችግር ባለባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎችም እንደ ወላጆችና ተማሪዎች ፈቃድ እንዲሁም እንደ አካባቢው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ሊከናወን ይችላል መባሉን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ፈተናው በአስር የትምህርት አይነቶች መዘጋጀቱና የኢኮኖሚክስ ፈተና በዘንድሮው መርሀ ግብር አለመካተቱንም ነው ዶክተር ዲላሞ የተናገሩት፡፡
ፈተና የሚወስዱት ተማሪዎች ካለፈው ዓመት በእጥፍ መጨምሩን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ዝግጀቱም በዚያው ደረጃ መደረጉን ተናግረዋል።
ከጸጥታ አንጻር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ባለመድረሳቸው ምክንያት የዘንድሮው ፈተናም ቀደም ሲል እንደነበረው በወረቀት ይከናወናል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version